የቀድሞው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ ከበደ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሆናቸው ታውቋል፡፡

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ የቀድሞውን የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ ከበደን፣ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ እንደገና መምረጡ ታወቀ፡፡ አቶ ሔኖክ የንብ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያገለግሉ ከቦርዱ የቀረበላቸውን ጥያቄ በመቀበላቸው፣ የንብ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሹመቱ…

ዘመን ባንክ በ2016 በጀት ዓመት 3.77 ቢሊዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ፡፡

ዘመን ባንክ በ2016 በጀት ዓመት ከግብር በፊት 3.77 ቢሊዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ፡፡ ዘመን ባንክ 16ኛ የባለአክስዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ሲያካሂድ  በ2016 (እ. አ. አ 2023/24) በጀት ዓመት ከግብር በፊት 3.77 ቢሊዮን ብር ማትረፉንና የአንድ አክሲዮን ትርፍ 37.6 በመቶ መሆኑን በሚሌኒየም…

ዘመን ኢንሹራንስ ኩባንያ ትርፉን ከ3 እጥፍ በላይ ማሳደጉን አስታወቀ፡፡

ዘመን ኢንሹራንስ ኩባንያ ዓመታዊ ትርፉን ከ3 እጥፍ በላይ ማሳደጉን አስታወቀ፡፡ ኩባንያው የ2016 የሒሳብ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን በተመለከተ ለሪፖርተር እንዳሳወቀው፣ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 181.3 ሚሊዮን ብር አትርፏል፡፡ ከታክስ በኋላ ያገኘው የትርፍ መጠን 151.3 ሚሊዮን ብር መሆኑን የኩባንያው ዓመታዊ ሪፖርት…

በነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተገለጸ፡፡

በነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተገለጸ፡፡ ከመስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ የሚተገበር በሁሉም የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አንዷለም አድማሴን የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አድርጎ ሾሟል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ፣ የቀድሞውን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዷለም አድማሴን የውጭ ግንኙነት ሃላፊው አድርጎ ሾሟል። አንዷለም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ደቡብ ሱዳን ውስጥ ከሌሎች ግለሰቦች ጋር ያቋቋሙትን አንድ አዲስ የቴሌኮም ኩባንያ በሃላፊነት በመምራት ላይ ነበሩ::

የቁም እንስሳት ወጪ ንግድ ወደ ጅቡቲ በባቡር ማጓጓዝ ተጀምሯል::

የቁም እንስሳት ወጪ ንግድ ወደ ጅቡቲ በባቡር ማጓጓዝ ተጀምሯል:: ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዳማ ወደ ጂቡቲ የቁም እንስሳት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ይፋ ሲደረየባቡር ትራንስፖርት ከዚህ በፊት ወደ ሀገር ውስጥ ገቢ ምርቶችን ለማስገባት ብቻ የሚያገለግል ነበር፡፡ አገልግሎቱ በባቡር መጀምሩ የወጪ ንግድ ገቢ ግኝታችንን…