
ዘመን ባንክ በ2016 በጀት ዓመት ከግብር በፊት 3.77 ቢሊዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ፡፡
ዘመን ባንክ 16ኛ የባለአክስዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ሲያካሂድ በ2016 (እ. አ. አ 2023/24) በጀት ዓመት ከግብር በፊት 3.77 ቢሊዮን ብር ማትረፉንና የአንድ አክሲዮን ትርፍ 37.6 በመቶ መሆኑን በሚሌኒየም አዳራሽ በተካሄደው 16ኛ የባለአክስዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ አስታውቋል፡፡
ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት እቅዱን ሙሉ በሙሉ በማሳካት ያገኘው ትርፍ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ1.01 ቢሊየን ብር ወይም በ36.8 በመቶ ብልጫ አለው፡፡
ባለፉት አምስት ዓመታት ባንኩ በአማካይ ለአንድ አክሲዮን የከፈለው ትርፍ 44.28 በመቶ ደርሷል ሲል በማኅበራዊ የትስስር ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡

