የቀድሞው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ ከበደ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሆናቸው ታውቋል፡፡

Spread the love

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ የቀድሞውን የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ ከበደን፣ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ እንደገና መምረጡ ታወቀ፡፡

አቶ ሔኖክ የንብ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያገለግሉ ከቦርዱ የቀረበላቸውን ጥያቄ በመቀበላቸው፣ የንብ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሹመቱ እንዲፀድቅለት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማመልከቱ ታውቋል፡፡

ንብ ባንክ ከስድስት ወራት በፊት አቶ ሔኖክን ለዋና ሥራ አስፈጻሚነት ዕጩ አድርጎ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም፣ በወቅቱ ብሔራዊ ባንክ ሹመቱን እንዳላፀደቀው ይታወሳል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ሹመታቸውን ያላፀደቀው ከአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚነታቸው እንዲነሱ የተደረጉበት ምክንያት ሊጣራ ይገባል ተብሎ እንደነበር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሆኖም አቶ ሔኖክ ከአማራ ባንክ የለቀቁበት ምክንያት አግባብ እንዳልነበር ከሥራ ሲሰናበቱ በአማራ ባንክ ቦርድ የተጻፈባቸው ደብዳቤ እሳቸውን የማይገልጽ መሆኑን በማመልከት ለብሔራዊ ባንክ ባቀረቡ አቤቱታ መሠረት፣ በአማራ ባንክ የተጻፈባቸውን ደብዳቤ መሠረት ያደረገው ዕግድ በብሔራዊ ባንክ ተነስቶላቸዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ንብ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ መርጧቸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *