የሲሚንቶ ዋጋ በሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎች እንዲወሰን ተደረገ

Spread the love

የሲሚንቶ ዋጋ በሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎች እንዲወሰን ተደረገ

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለሲሚንቶ ፋብሪካ ድርጅቶች በጻፈው ደብዳቤ ከጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ምርታቸውን በፍትሃዊ ዋጋ  እንዲያቀርቡ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም የሲሚንቶ ምርት የፋብሪካ መሸጫ ዋጋ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተወሰነ ለገበያ ሲሰራጭ የቆየ ቢሆንም በአዲሱ የአሰራር ሂደት ግን አምራች ፋብሪካዎች ሙሉ ሀላፊነቱን በመውሰድ በነጻነት ምርታቸውን ለገበያ እንዲያቀርቡ እና ገበያውን እንዲያረጋጉ ሃላፊነት መስጠቱን ሚኒስቴሩ እውቁልኝ ብሏል፡፡

የሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ የተሰጣቸውን ሀላፊነት በተጠያቂነት ስሜት እና በፍትሃዊ የዋጋ ተመን ማህበረሰቡን እንዲያገለግሉም መወሰኑን ገልጾ ከዚህ ቀደም አገልግሎት ላይ ይውል የነበረውን መመሪያ 940/2015 ማንሳቱን ይፋ አድርጓል፡፡

edited24212:27

Leave a comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *