ታላቁ ሩጫ በአዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡

Spread the love

ታላቁ ሩጫ በአዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡

በወንዶች አትሌት ቢንያም መሐሪና በሴቶች አትሌት አሳየች አይቼው ደግሞ የውድድሩ አሸናፊዎች ናቸው።

50 ሺህ ተወዳዳሪዎች የተሳተፉበት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር የተካሄደው “የተመጣጠነ ምግብ ለሁሉም ህፃናት” በሚል መሪ ቃል መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ ነው።

ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሣ፣ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካን ጨምሮ በርካታ ዲፕሎማቶችና የሀገር ውስጥና ውጭ ሀገር አትሌቶች ተገኝተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *