የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር 2 በኤሌክትሪክ ሀይል የሚንቀሳቀሱ አውቶብሶችን ተረክቧል።

Spread the love

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳድር በበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የደብረ ብርሃን መኪና መገጣጠሚያ የተገጣጠሙ 2ት በኤሌክትሪክ ሀይል የሚንቀሳቀሱ የከተማ አውቶብሶችን ተረክቧል።

በርክክቡ ወቅት የተገኙት የከተማ አስተዳድሩ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሽት እንደገለጽት መኪና መገጣጠሚያው ቦታ በተረከበት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ ምርት የጀመረ በመሆኑ ከተማ አስተዳድሩ ልዬ ምስጋና አለው ብለዋል።

በተለይ የፋብሪካው ስራ መጀመር የከተማ አስተዳድሩ ለሠራተኞቹ ቃል የገባውን ተሽከርካሪ የማቅረብ እቅድ በአጭር ጊዜ ገጣጣሞ በመረከባችን ትልቅ ምስጋና አለን ብለዋል።

ወደፊትም ተጨማሪ ተሽከርካሪዎችን ለማሠራት እቅድ አለን ሲሉ ገልጸዋል ።

የፋብሪካው ስራ አስኪያጂ አቶ ሙሃመድ አህመድ በበኩላቸው ፋብሪካው ከገጣጠማችው የመጀመሪያ ምርቶች ውስጥ ለደብረ ብርሃን ከተማ በማስረከባችን ትልቅ ደስታ ተሰምቶናል ያሉ ሲሆን ፋብሪካው በሀገር ደረጃ የሚታየውን የህዝብ ትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ በስፋት እየተንቀሳቀሰ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

የደብረ ብርሃን መኪና መገጣጠሚያ በቅርቡም የገጣጠማቸውን 4ት በኤሌክትሪክ ሀይል የሚንቀሳቀሱ የከተማ አውቶብሶችን ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስረክቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *