
በአፍሪካ ፈር ቀዳጅ የቴሌኮም ኦፕሬተር የሆነውና ታላቋን ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ለ130 ዓመታት በኩራት ሲያገለግል የቆየው የኢትዮ ቴሌኮም 10% አክሲዮን ሽያጭ በዛሬው ዕለት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድበይፋ መጀመሩን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው!
በዚህ መሰረት 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች ለኢትዮጵያውን ከዛሬ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም በቴሌብር ሱፐርአፕ ለሽያጭ የቀረበ ሲሆን የአክሲዮን ሽያጩ ሰፊውን ማህበረሰብ ያካተተ እንዲሆን አነስተኛውን የሼር ዋጋ መጠን 9,900 ብር (33 አክስዮኖች) በማድረግ ከፍተኛውን የአክስዮን መጠን ደግሞ 999,900 ብር ወይም (3,333 አክስዮኖች) ተደርጓል፡፡
በዚህ ታሪካዊ አጋጣሚ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በነገዋ ሀገራችን ልዩ የኢንቨስትመንት እድል ተጠቅመው በአገሪቱ ካሉት ግዙፍ ተቋማት መካከል የአንጋፋው ኩባንያ ባለአክሲዮን እንዲሆኑ እና የኢትዮ ቴሌኮምን ቀጣይ እድገት እንዲደግፉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

