
በቻይና 378 ሺ የሰው ሰራሽ አስተውሎት/(Artificial intelligence) የፈጠራ መብቶች ተመዝግበዋል፡፡
ይህ የተገለጸው የዓለም የኢንተርኔት ጉባኤ በቻይና ዘጂያንግ ግዛት ውጀን ከተማ ሲካሄድ ነው፡፡
ከ1800 በላይ ታዳሚዎች በተገኙበት የተካሄደው ጉባኤው ተሳታፊዎቹ ከ130 ሀገራትና ክፍለ አህጉራት የተገኙ ናቸው፡፡
ለአራት ቀናት የቆየው ጉባኤ “Embracing a People-Centered and AI-For-Good Digital Future – Building a Community with a Shared Future in Cyberspace,” በሚል መሪ ሀሳብ ሲካሄድ በዓለም የልማት ኢንሼቭ፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ እንዲሁም ሌሎች ተግባራትን ጨምሮ ከ24 በላይ መለስተኛ ፎረሞች ተከናውነውበታል ብሏል ሲጂቲኤን በዘገባው፡፡

ከ40 በላይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማሳያዎች ለእይታ የቀረቡበት ኤግዚቢሽን ሲካሄድ ሩሲያ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይና ሲንጋፖርን ጨምሮ ከ53 ሀገራት የተውጣጡ ኢንተርፕራይዞች ተሳትፈውበታል፡፡
የቻይና የሳይበር ስፔስ ጥናት አካደሚ በጉባኤው ይፋ ባደረገው ሪፖርት መሰረት የሀገሪቱ ፋብሪካዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ ሲሆን 10 ሺዎች እንደሚደርሱም ተነስቷል፡፡
ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ በቻይና ብቻ 378 ሺ የሚሆኑ ስራ ላይ የዋሉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የፈጠራ መብቶች መመዝገባቸው ሲጠቀስ ከዓለም አማካይ በ1 ነጥብ 4 እጥፍ ከፍ ያለ ስለመሆኑም ዘገባው አትቷል፡፡
