
ሺንትስ የጨርቃጨርቅ ኩባንያ ለሰራተኞቹ ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች ነገ ያስመርቃል::
በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው ሺንትስ ጋርመንት ለሰራተኞቹ ያስገነባቸውን የህጻናት ማቆያ እና የሰራተኞች የመዝናኛ ማዕከላት የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች፤ የኩባንያው ባለቤቶችና እንግዶች በተገኙበት በነገው እለት ያስመርቃል፡፡

ኩባንያው ከ8ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሮ እየሰራ ሲሆን ዘመናዊ መኖሪያ፤ የትራንስፖርትና የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ምቹ የስራ ከባቢን ፈጥሯል፡፡
ሺንትስ ጋርመንት እና ቴክስታይል አለምአቀፍ የስፖርት ትጥቆችና አልባሳትን በማምረት ለአሜሪካ ፤ለአውሮፓ እንዲሁም ለእስያ ሃገራት ምርቶቹን የሚያቀርብ የደቡብ ኮሪያ ኩባንያ ነዉ ፡፡
መረጃው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን
