
የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ያመረታቸውን 100 ፒካፕ መኪኖችን ለመንግስት ግዢ አገልግሎት አስረከበ።
በኢትዮ ኢንጂነር ግሩፕ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንደስትሪ እና በመንግስት ግዢ አገልግሎት መካከል የN-7 ፒካፕ ተሽከርካሪ ርክክብ እና ፊርማ ተካሂዷል ።
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች በመገጣጠም ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ በትራንስፖርት ዘርፉ የራሱን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል ።
በቢሾፍቱ ማምረቻ ኢንደስትሪ የገጣጠማቸውን 100 N-7 ፒካፕ ተሽከርካሪዎችን ነው ለመንግስት ግዢ አገልግሎት ያስረከበው ።

የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ አጋጥሞት ከነበረው የፋይናንስ ችግር በማገገም እንዲሁም ሪፎርም ከተደረገ በሃላ ለመጀመሪያ ያመረታቸው መኪኖች ማስረከቡ ተገልጿል ።
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስኪያጅ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንደስትሪ ገጥሞት በነበረው የፋይናንስ ችግር ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ማምረት እንዳልቻለ ገልፀው በቀጣይ በሙሉ አቅሙ የተለያዩ መኪኖችን ከመገጣጠም ባለፈ በሀገር ውስጥ ለማምረት እቅድ መያዙን ገልጸዋል ።
NBC Ethiopia
