ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ምርቱን ለገበያ ማቅረብ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

የማምረት ሥራውን በቅርቡ የጀመረው የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ምርቱን ለገበያ ማቅረብ መጀመሩን በመገናኛ ገጹ አስታውቋል፡፡
ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ግንባታውን በማጠናቀቅና የማምረት ሥራውን በፍጥነት በመጀመር ምርቱን በቶሎ ወደ ገበያ በማውጣት በሀገር ደረጃ ያለውን የሲሚንቶ ገበያ ለማረጋጋትና እንደሀገር የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት ለመወጣት እየሰራ ስለመሆኑም ገልጧል፡፡

የምርት ጥራትን በተመለከተ ዘመናዊና የተደራጀ ላቡራቶሪ በመገንባትና ባለሙያ በማሟላት የጥራት መስፈርት ማረጋገጫ ስለማግኘቱም በፌስቡክ ገጹ አስፍሯል፡፡
ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶክተር) በቅርቡ ተመርቆ ስራ መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡

