
በኡጋንዳ እና ታንዛኒያ መካከል የሚገነባው የነዳጅ ማስተላለፊያ ፕሮጀክት ግንባታ የፋይናንስ እጥረት ማጋጠሙ ተነገሩ፡፡
በ5 ቢሊየን ፤ዶላር የሚገነባው የምስራቅ አፍሪካው ግዙፍ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ በሁለቱ ሀገራት የጋራ ድጋፍ እንዲሁም በቶታል ኢነርጂስ እና በቻይናው ናሽናል ኦፍሾር ኦይል ኮርፖሬሽን ድጋፍ ሊገነባ የተጀመረ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ ከአካባቢ መራቆትና ተያያዥ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ጋር በተያያዘ እንደ ባርክሌይስ ያሉ የአውሮፓ ባንኮች ድጋፍ ለማድረግ አለመፈለጋቸውን ተከትሎ ድጋፍ ሊያደርጉ የነበሩት ድርጅቶች ድጋፋቸውን ማቋረጣቸው ተሰምቷል፡፡

ይህንን ተከትሎ የቻይና ድጋፍ አድራጊ አካላት እንዲያግዙ የተጠየቀ ሲሆን ገንዘብ ፈሰስ ማድረግ ያቆመው ቶታል ኢነርጂስ 400 ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ በጀት ሊሰጥ እንደሚችልም ተጠቁሟል፡፡
ፕሮጀክቱን ለማስቀጠል ኡጋንዳ የ45 ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ ገንዘብ ለማውጣት የተስማማች ሲሆን ታምዛኒያም ተመሳሳይ የገንዘብ መጠን ለፕሮጀክቱ ታቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ፕሮጀክቱ ከኡጋንዳ የአልበርታ ኃይቅ አካባቢ የነዳጅ ክምችት ወደ ታንዛኒያ ታንጋ ወደብ በቀጥታ የሚያስተላልፍ ሲሆን በምስራቅ አፍሪካ ግዙፉ የነዳጅ ማስተላለፊያ ፕሮጀክት መሆኑን ቢዝነስ ኢንሳይደርአ ፍሪካ አስፍሯል፡፡
