በላይነህ ክንዴ ግሩፕ በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን አስረከበ፡፡

Spread the love

በላይነህ ክንዴ ግሩፕ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የገጣጠማቸውን በኤሌክትሪክ ሀይል የሚንቀሳቀሱ የከተማና መካከለኛ አውቶብሶችን አስረከበ ።

በርክክቡ ወቅት የተገኙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እንደተናገሩት

በአሁኑ ወቅት መንግሥት በፖሊሲ ደረጃ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተቋሙ ፖሊሲውን ለመደገፍና በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾችን ለማበረታታት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ኢንጂነር አሸብር አክለውም የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ስኬት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካደረጉ ተቋማት ውስጥ አንዱ ነው ብለዋል።

የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ባለቤትና የቦርድ ሰብሳቢ አቶ በላይነህ ክንዴ በበኩላቸው ድርጅታቸው በአውቶሞቲቭ መገጣጠሚያና የምግብ ማቀነባበሪያ ዘርፎች ላይ እየተሳተፈ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ቢኬጂ ከዚህ በፊት ይታወቅበት ከነበረው የነዳጅ ተሸከርካሪዎች የመገጣጠም ሥራን በማስፋት ካለፈው አመት ጀምሮ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን በመገጣጠም በሀገር ደረጃ የራሱን አሻራ እያሠረፈ መሆኑን አስረድተዋል።

አቶ በላይነህ አክለውም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በቢኬጂ የተገጣጠሙትን የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች መጠቀም መጀመሩ ሌሎች ተቋማትና ግለሰቦች በተሸከርካሪዎቹ ላይ አመኔታ እንዲኖራቸው ዕድል እንደሚፈጥርም አመልክተዋል፡፡

የተሸከርካሪዎቹ ባትሪ ለ15 ዓመታት እንደሚያገለግል የጠቀሱት አቶ በላይነህ ኩባንያው ለባትሪ የ8 ዓመት እንዲሁም ለሞተር የ5 ዓመት ዋስትና እንደሚሰጥም ተናግረዋል።

ቢኬጂ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *