34 ሀገራት ብሪክስን ለመቀላቀል መጠየቃቸውን የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ተናገሩ፡፡
ከቀናት በፊት የብሪክስ አባል ሀገራት በሩሲያ ባደረጉት ስብሰባ ላይ የዚህ ዓመት የብሪክስ ፕሬዚደንት የሆነችው ሩሲያ በርካታ ሀገራት ድርጅቱን ለመቀላቀል ፍላጎት አሳይዋል ብላለች፡፡
በቅዱስ ፒተርስበርግ ኮንስታንቲኖቭስኪ ቤተ መንግስት የአባል ሀገራትን ተወካዮች ያገኙት ፕሬዚደንቱ በርካታ ሀገራት የመቀላቀል ጥያቄ እያቀረቡ ሲሆን ይህንን እንደ መልካም እድል መውሰድ ይገባል፤ ግን ደግሞ አሰራር ማበጀት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የብሪክስ የጸጥታ ጉዳዮች ጉባኤ ለ2 ቀናት ሲካሄ ስ ዓለም መጻኢ አሰላለፍ ውይይቶች ስመደረጋቸው ተሰምቷል፡፡


