ከ50 ሺ ብር እስከ 3 ሚሊየን ብር ከጳጉሜን የገንዘብ ቁ/ብ/ኅ ሥራ ማኅበር

Spread the love

በተከታታይ ለ6 ወራት ቁጠባ የቆጠቡ ደንበኞ እስከ 3 ሚሊየን ብር ብድር እንደሚሰጥ ጳጉሜን የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር የኅብረት ስራ ማህበር አስታወቀ፡፡

አቶ ዘላለም ጌታነህ የጳጉሜን የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅ/ስራ ማህበር ስራ አስኪያጅ ናቸው፡፡

ጳጉሜን በተለይም ለዝቅተኛው የህብረተሰብ ክፍል ገንዘብን በቁጠባ በማሰባሰብ መልሶ በማበደር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማምጣት እየሰራ ሲሆን ባንክ ተደራሽ የማያደርጋቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ማድረግ ነው ተብሏል፡፡

በ283 አባላት የተመሰረተ ሲሆን አሁን ከ600 በላይ አባላት ያሉት የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር የኅብረት ስራ ማህበር ነው፡፡

ማኅበሩ የተለያዩ የብድር አይነቶች ሲኖሩት ከ50 ሺ ብር እስከ 3 ሚሊየን ብር ማበደር መቻሉንም ዋና ስራ አስኪያጁ ዘላለም ጌታነህ ለኢትዮጵያን ቢዝነስ ገልጸዋል፡፡

በቴክኖሎጂ የታገዘ ገንዘብ አሳሰብና ደረሰኝ አሰጣጥ አለን የሚሉት ስራ አስኪጁ የህጻናት ብድር፣ የመኪና፣ የቤት፣ የክብረ በዓላት የመሳሰሉት የብድር አይነቶች ስለመኖራቸውም ገልጸዋል፡፡

የቡድን ቁጠባ አንዱ አዲስ የሚሰራበት የቁጠባ እና ብድር አይነት መሆኑን የተናገሩት አቶ ዘላለም እንደ ጊዮርጊስና ቡና ያሉ ክለቦች ላይ ያሉ ተጨዋቾች በቡድን መቆጠብ ስለመጀመራቸውም ጠቁመዋል፡፡

ለእናቶችና ለወጣቶች ከማበደር ባሻገር የስራ እድል ትስስር እንደሚፈጥሩ የገለጹት ስራ አስኪያጁ በአረብ ሀገራት የሚገኙ የቤት ሰራተኞችና ሌሎች ግለሰቦች በማህበሩ መሰረት ገንዘባቸውን እንዲቆጥቡ እና እንዲበደሩ የማመቻቸት ስራዎች እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

ለትምህርትና ለመሳሰሉት የቁጠባ እና ብድር አገልግሎት መመቻቸቱን የተናገሩት አቶ ዘላለም ተማሪዎች የተምህርት እድል ቢያገኙ በገንዘብ እጥረት እንዳይገሩ ምቹ ሁኔታ የመፍጠር ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የተሻለ ወለድ እንደሚከፍል የገለጹት ስራ አስኪያጁ ከ6 ወራት በላይ የቆጠቡ አካላት እስከ 3 ሚሊየን ብር ብድር እየተሰጠ መሆኑንና እስከ 3 ወራት በተከታታይ ለቆጠቡ ደግሞ ከ50 ሺ ብር እስከ ግማሽ ሚሊየን ብር ብድር እንደሚመቻችም ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *