ጤፍ ከኢትዮጵያ እጅ እየወጣ ስለመሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

Spread the love

ጤፍ ከኢትዮጵያ እጅ እየወጣ ስለመሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት ሁሉም ምርት ሁሉም ስፍራ የሚገኝበት ነው፡፡ ለዚህም ነው ጤፍ መነሻውና መብቀያው ኢትዮጵያ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ከ25 በላይ ሀገራት ጤፍን እንደሚያመርቱት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ኢትዮጵያ እስከ 98 በመቶ የሚሆነውን የጤፍ ምርት እንደምታመርት መረጃዎች ቢያመለክቱም ጎረቤት ኤርትራን ጨምሮ በርካታ ሀገራት እያመረቱ መሆናቸው ይነገራል፡፡ ለአብነትም አሜሪካ፣ አውስትራሊያ፣ ስፔን፣ ህንድና

ካናዳ፣ ቻይና፣ ኔዘርላንድ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ እንግሊሊና የመሳሰሉት ሀገራት ጤፍን እያረቱ ሲሆን እንደ ኡጋንዳ እና ካሜሩን ያሉ ሀገራት ደግሞ ከቅርብ አመታት ወዲህ ጤፍ በማምረት ላይ የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው፡፡

ጤፍ ለጤና አስፈላጊ እና ማዕድናትን አመጣጥኖ የያዘ የምግብ እህል ሲሆን በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ደግሞ ተዘውትሮ የሚበላ ምግብ ነው፡፡ በውስጡ እንደ ስንዴ ባሉ ሰብሎች ውስጥ የሚገኘው ግሉትን የተሰኘው ተለጣጭ የፕሮቲን ውህድ የሌለው በመሆኑ እጅግ ተመራጭ የምግብ ግብዓት ስለመሆኑም የስ ምግብ ተመራማሪዎች ይጠቅሳሉ፡፡

አስላጊ ፋይበር፣ ብረት፣ ፕሮቲን እ ሌሎች ንጥረ ነገሮችን በመያዙ ተመራጭ እየሆነ ስለመጣ አሁን በብዛት እና በብዙ ሀገራት እንዲመረት ስማድረጉም በምክንያትነት ይጠቀሳል፡፡

ጤፍ በኢትዮጵያ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ4 ሺ ዓመታት ላለፈ ጊዜ ጀምሮ ይመረት እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2003 አንድ የኔዘርላንድ ኩባንያ የጤፍ ዱቄትን ከመፍጨት፣ ከማስቀመጥ ጥቅም ላይ ከማዋል አንጻር የባለቤትነት መብት አለኝ በሚል እስከ መጠየቅ ደርሶ በአውሮፓ እውቅና አግኝቶ ነበር፡፡ ባለቤቷ ኢትዮጵያ ባለችበት እንደዚህ አይነት ዓለም አቀፍ የመብትና ጥቅም መንጠቅ ተግባራት መወገዝ እንደሚገባቸው ብዙዎች ሲጠቅሱ ቢደመጥም የባለቤትነት መብቱ እስካሁን በአንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት ግን እንዳለ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ላዚህ ነው ዊኪፒዲያ የተሰኘው ነጻ ኢንሳይክሎፒዲያ አሁንም የጤፍ ዱቄትን ያገኘው ጃን ሮሰን ነው ሲል በሚያስቅ መልኩ አስፍሮት ይገኛል፡፡ እንደዚህ አይነት አይን ያወጣ ዘረፋ እንዲቆም መስራት ያስፈልጋል እላለን፡፡

ከኢትዮጵያ ውጭ ጤፍን ማምረት የጀመሩ ሀገራት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዘው ሲያመርቱ መመልከት በተለይም ምርቱን በገፍ ሊያቀርቡ ከመቻላቸው አንጻር ለኢትዮጵያ ተወዳዳሪ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እንዲያውም ከአመት በፊት ተስፋ ዳራር የተሰኘ ሰው ጤፍን በአሜሪካ አምርተን ወደ ምስራቅ አፍሪካ በእርዳታ ምርትነት እንልካን ሲል በሚዲያ ሲነጋር እንደነበር የምናስታውሰው ነው፡፡

በአሜሪካ ጤፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቀው እኤአ በ1980ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ሲሆን ከ25 በላይ ግዛቶች ጤፍ እንደሚያመርቱ ይገመታል፡፡ እንደ ኢዳሆ፣ ካንሳስ እና ኔብራስካ ያሉ ግዛቶች ደግሞ በስፋት በማምረት የሚታወቁ ሲሆን ለእንስሳት ምግብነት እንዲሁም ለኢትዮጵያውያን በብዛት እንደሚቀርብ ነው የሚታወቀው፡፡

በአብዛኛው ጤፍን የተላመዱ ሀገራት ስንመለከት ደግሞ ምርቱን በማላመድ ትልቁን ድርሻ የሚወስዱት ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ናቸው፡፡

በጤፍ ዙሪያ በተለይም ለባለቤቷ ኢትዮጵያ በርካታ የገበያ እና የመሳሰሉ ስራዎች እንዳሉባት የሚያስገነዝቡ ወገኖች አሉ፡፡ ከዓለም ገበያ ጋር የማቀራረብ፣ የአመራረት ሂደቱን የማዘመን የበለጠ ተጠቃሚ መሆን የምትችልበትን እድል መመልከት እንደሚገባም ይመከራል፡፡

ለአብነትም ጤፍን በብዛት በማምረት እየተጠቀሰች ያለችው ስፔን ማምረት ከጀመረች ከአስር ዓመታት በላይ ያስቆጠረች ሲሆን ምርቱን ወደ ውጭ በመላክም ትታወቃለች፡፡

እስከ 1 ሺ ቶን ጤፍ የምታመርተው ስፔን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የአውሮፓን ገበያ የመቆጣጠር እድል እንዳላትም እየተነገረ ነው፡፡

ጤፍ ዋነኛ የሀገሪቱ ህዝብ ምግብ ከመሆኑ የተነሳ የገበያውን ሁኔታ የተረጋጋ ለማድረግ የጤፍ የወጭ ንግድ እንዳይደረግ ቢታገድም የእንጀራ ንግድ ግን እንደተጧጧፈ the Open Agriculture Journal, 2018, ቅጽ 12 ላይ Teff, A Rising Global Crop: Current Status of Teff Production and Value Chain በሚለው ጥናቱ አትቷል፡፡ እንዲያውም ይላል መጽሔቱ እንደ ዩናይትድ አረብ ኢምሬቶች፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ባህሬንና ስዊደምን ያሉ ሀገራት ግንባር ቀደም የደረቅ እንጀራ መዳረሻ ሀገራት ናቸው ይላል፡፡

የእንጀራን ሁለንተናዊ የጤለና ጥቅም የሚገልጸው ጥናቱ ኢትዮጵያ የዓለምን ከፍተኛ ድርሻ የያዘች ሀገር እንደመሆኗ የጤፍን ረመል መጠበቅ እንደሚያስፈልግ እንዲሁም በዓለም ገበያ አለማቅረቧንና አለማስተዋወቋን ተችቶ ሌሎች ሀገራት ግን በፍጥነት ወደ ገበያው እየገቡ ነው ሲል ያክላል፡፡

ጤፍ በምግብነት የዓለም ገበያን የተቆጣጠሩትን በቆሎ፣ ስንዴና ሩዝን ሊተካ የሚችል እና ለዓለም ህዝብ ትልቅ የምግብ አቅቦት ሊኖረው የሚችል ስለመሆኑም ነው የተወሳው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *