
“ኢትዮ- ግሪን ሞቢሊቲ 2024” የተሸከርካሪዎች አውደ-ርዕይ እየተካሄደ ነው፡፡
ይህ ዓለም አቀፍ ዐውደ ርዕይ በሁዋጂያን ኢንተርናሽናል ላይት ኢንዱስትሪ ሲቲ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የተከፈተ ሲሆን በሲምፖዚየሙ አስመጭዎች፣ ገጣጣሚዎች እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪና መሠረተ ልማት አምራቾችና አቅራቢዎች እየተሳተፉ ነው፡፡
የዘርፉን ተዋንያንን ያበረታታል የተባለው ይህ ዐውደ ርዕይ ነሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎን ነው የተከፈተው፡፡

በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው በዚህ ዓለም አቀፍ ዝግጅት ለታዳሽ የትራንስፖርት ዘርፍ ልዩ ትኩረት ስለመሰጠቱ ተጠቅሷል፡፡
በዝግጅቱም አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለእይታና ለሽያጭ የቀረቡ ሲሆን የባጃጅ፣ የብስክሌት፣ የባለ አራት እግርና ሌሎችም የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለእይታ ቀርበዋል፡፡
በላይነህ ክንዴ ግሩፕ፣ ካኪ ሞተርስ፣ ሳፊ፣ ሆራ ትሬዲንግ እና ሌሎችም ምርቶቻቸውን በኤግዚቢሽኑ ያቀረቡ ድርጅቶች ናቸው፡፡

