
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከግሉ ዘርፍ ጋር በማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርምና ግኝቶች ዙሪያ ከግሉ ዘርፍ ጋር ተወያዬ፡፡
ሚኒስትሯ ዶክተር ፍጹም አሰፋ ረጅም ሰዓት ወስደው ማብራሪያ በሰጡበት መድረክም ባለፉት ከስልሳ በላይ ዓመታት ኢኮኖሚው የነበረበትን ውጣ ውረድ አብራርተዋል፡፡

ባኣሁኑ ወቅትም ሀገሪቱ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ ስለመሆኗ ተናግረዋል ሚኒስትሯ፡፡
በኃይሌ ግራንድ ሆቴል በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሠፋ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱን ጨምሮ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ እንዲሁም ሌሎች እንግዶችና የተቋማትና ማኅበራት ተወካዮች ተገኝተዋል።
የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ ዋነኛ ተዋናይ መሆን እንዳበት የተጠቆመ ሲሆን በተለያዩ ዘርፎች የሚተዋሉ የኢኮኖሚ ማነቆዎችን ያነሱት ተሳታፊዎች በገንዘብ ሚኒስትሩና በሌሎችም ባለስልጣናት ማብራሪያ ተሰጥባቸዋል፡፡
