አጭር ቀሚስ አስለብሶ መስተንግዶ የሚያሰራ ሆቴል የ50 ሺህ ብር መቀጮ

Spread the love

በአዲስ አበባ ከተማ አጭር ቀሚስ አስለብሶ የመስተንግዶ ስራ የሚያሰራ ምግብ ቤት እና ሆቴል የ50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ የሚያስቀጣ የደንብ ረቂቅ ፀደቀ

ከጉልበት በላይ የሆነ አጭር ቀሚስ አስለብሶ የመስተንግዶ ስራ ያሰራ ሆቴል እና መሰል ተቋም እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡

በቢሮው የቱሪስት አገልግሎት ተቋማት ብቃት ማረጋገጥና ደረጃ ምደባ ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ይመር ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ቢሮዉ በአዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀፅ 22 ቁጥር 6-13 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዙሪያ ኢትዮጵያዊ ባህልና እሴት እየተሸረሸረ በመሆኑ የወጣዉ የደንብ ረቂቅ ፀድቋል።በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ፣ የገፅታና የውበት አጠባበቅ እንዲሁም የጌጣጌጥ አጠቃቀም ስነ-ስርዓት ላይ ቢሮዉ ያወጣዉ የደንብ ረቂቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት እንዲፀድቅ ተደርጓል።

from- ዳጉ_ጆርናል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *