
ኢትዮጵያዊው ሰዓሊ ወንድወሰን ከበደ የ2024 የአፍሪካ ፋሽንና ሥነ-ጥበብ ሽልማት ( AFAA ) ተሸላሚ ሆኗል።
ሰዓሊው በአፍሪካ ስልጣኔ፣ ባህል እና ፓን አፍሪካኒዝም እንዲሁም በኢትዮጵያ ስልጣኔ ፣ ባህል እና ማንነት ላይ በሠራቸው የስዕል ሥራዎች እና በተለያዩ ዓለማት በተሳተፈባቸው ዐውደ ርዕዮች ባገኛቸው እውቅናና ሽልማቶች መነሾነት ነው ተሸላሚ የሆነው።

የአፍሪካ ፋሽንና ሥነ-ጥበብ ሽልማት (AFRICAN FASHION & ART AWARD -AFAA ) ከዚህ ቀደም ለእነ ቺኒዋ አቼቤ፣ አለን ፔተን፣ የሚ አላዴ፣ ብሬንዳ ፋሴ እና ከሰዓሊያን እነ ቼሪ ሳምባ፣ አብዱላሂ ኮንቴ እና ኢብራሂም አል ሳላሂ ለመሳሰሉ አፍሪካውያን ዝነኞች ሽልማት አበርክቷል።
from- ከ የኔታ ቲዩብ
