
በበዓሉ ላይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘ አክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕማቶች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና የእምነቱ ተከታዮ ተገኝተዋል፡፡

የመስቀል በዓል ከሃይማኖታዊ ሥርዓቱ ባለፈ ለኢትዮጵያ የቱሪዝም አንዱ ሐብት ሲሆን በዓለም የባህል ቅርስና የሳይንስ ተቋም /በዩኒስኮ የማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበም ነው፡፡
የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ኃይማኖታዊና ባህላዊ ስን ስርዓቶች ሲከበር የቆየ ታላቅ ክብረ በዓል ነው፡፡


