ኬንያ ከምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት ውጭ የስኳር ግዥ እንዳይካሄድ አገደች፡፡

የሀገሪቱ መንግስት ወደ ኬንያ የሚገባ ስኳር ከምስራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ እንዲሁም ከደቡብና ምስራቅ አፍሪካ የጋራ ገበያ ኮሜሳ ውጭ እንዳይዛ ክልከላ መጣሏን ይፋ አድርጋለች፡፡
ሀገሪቱ ያላት የስኳር ፍጆታ ከ9 መቶ ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ ሲሆን አሁን ግን እየተመረተ ያለው ስምንት መቶ ሺ ሜትሪክ ቶን አካባቢ ነው ሲል የሀገሪቱ ግብርና እና እንስሳት ሀብት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ከ16 ፋብሪካዎች እስከ 7 መቶ ሺ ሜትሪክ ቶን ስኳር በየዓመቱ ስታመርት የነበረችው ኬንያ አሁን ግ መሻሻል ማሳየቷን ጠቁሟል ሚኒስቴሩ፡፡
ለሚቀርበው ስኳር ጉድለት ከሌሎች ሀገራት እንዲገባ ተፈቅዶ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ከምራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት ውጭ ግዥ እንዳይከናወን ማገዷን አስታውቃለች፡፡

ህገ ወጥ የስኳር ዝውውርን ለመቆጣጠር ከፍታ የጸጥታ ቁጥጥር ስምሪት ማድጓን ያስታወቀችው ኬንያ በነጻ ንግድ ቀጠና የተቀመጡ ፕሮቶኮሎችን ባከበረ መልኩ ስኳር ከምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት ብቻ እንዲገባ ስለመወሰኗ ነው የተነገረው፡፡
ኮሜሳ 21 አባል ሀገራትን የያዘ ሲሆን የምስራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህረሰብ ደግሞ 8 ሀገራትን ያቀፉ ቀጠናዊ ተቋማት ናቸው፡፡ ዘ ኢስት አፍሪካን
