
ማክስ ዌል ሳንጉላኒ ቺኩምቡተሶ ይባላል፡፡ በሀገረ ዚምባብዌ ማዞየ በተባለች አነስተኛ ከተማ በ1980 የተወለደ የ44 ዓመት ጎልማሳ ነው፡፡
በትምህርት ደረጃው ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያቋረጠ ሰው ነው፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የዓለምን መልክ የቄረ የፈጠራ ውጤት ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ በዚህ ፈጠራው የተለያዩ አካላት በተቀናቃኝነት እንዲመለከቱት ስለማድረጉ እየተወራ ነው፡፡
ባኣሁኑ ወቅት በዚምባብዌ ፕሬዚደንት ልዩ ጥበቃ እንደሚደረግለት የሚነገረው ቺኩምቡትሶ ራሱን በራሱ ኃይል የሚሰጥ ከነዳጅም ሆነ ከኤሌክትሪክ ነጻ የሆነ ቅንጡ መኪና በመስራት እንደ ቴስላ ያሉ የዓለም የቅንጡ ሚና አምራች ኩባንያዎች እና እንደ ኤለን መስክ ያሉ የቢዝነስ ሰዎችን ያበሳጨ ሰው ሆኗል፡፡
ለዓለም አዲስ ብስራት ይዞ የመጣውና ተሰርቶ ስኬታማ የሆነው በሬዲዮ ሞገድ የሚሰራው ቅንጡ መኪና እና ሞተር ብስክሌት አሁን ዓለምን እያጋገረ ያለ አስደናቂ ፈጠራ ሲሆን በአፍሪካዊ መሰራቱ ደግሞ አዲስ አይን ከፋች የይቻላል መንፈስ የፈጠረ ስለመሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
ቺኩምቡትሶ መኪና መስራቱ ብቻ ሳይሆን በቀን 30 ሺ ተሸ ከርካሪዎችን ገጣጥሞ ለደንበኞቹ ማቅረብ የሚችል መገጣጠሚያ መሰራቱ ደግሞ በዓመት እስ 10 ሚሊየን ተሸከርካሪዎችን ለገበያ ማቅረብ ያስችለዋል፡፡
ካኣሁኑ በርካታ የስራ ትዕዛዞች እየጎረፉ መሆኑ የተነገረለት የዚምባብዌው የመኪና መገጣጠሚያ የፈጠራ ስራ ነዳጅንም ሆነ እጅግ የዘመነ የተባለላቸውን የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን አሁኑኑ ተረት ያደረገ ነው፡፡
በኃይል አቅርቦትና በትራንስፖርት ዘርፉ እጅግ አስደናቂ የሆነው ይህ የፈጠራ ውጤት በነዳጅ ላይ ተንጠለጠለውን የትራንስፖርት ስርዓት በመቀየር ሌላ ከፍታ ላይ ያደርሰዋል፡፡

ሴት የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ዘመናዊ ተሸከርካሪ ከቻይና ኩባንያ ጋር በመሆን የመኪናውን ክፍል የሚገጣጥም ሲሆን በሰዓት እስ 220 ኪሎሜትር መጓዝ የሚችል ልዩ መኪና ነው፡፡
መኪናው ራሱን ፓርክ የሚያደርግ ስርዓት የተገጠመለት እና እጅግ የዘመነ የማሽከርከር ስርዓት ያለው ሆኖ በ14 ሺ ዶላር ወይም በአሁኑ የኢትዮጵያ ገንዘብ ከ2 ሚሊየን ብች በታች ለሽያጭ ቀርቧል፡፡
የዚምባብዌው ፕሬዚዳንት እንደዚህ ወርቅ እጅ ያላቸውን ዜጎች መንከባከብ ይገባል- በራሳቸው ዜጎች የተሰራች ሀገር ልትኖረን ያስፈልጋል ሲሉ በሀገርኛው ቋንቋ -ኒካ ኢኖቫኳ ኔቨን ቫዮ- ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በሀገሪቱ ግዙፍ የመኪና ማምረቻ መሰራት እንዳለበት ያብራሩት ፕሬዚዳንቱም ዚምባብዌ የዓለም የታዳሽ ኃይል አቅርቦት ማዕከል እንደምትሆን በፈጠራው በመተማመን አብራርተዋል፡፡
በማይከሮሶኒክ የኃይል ስርዓት ራሱን በራሱ ኃይል እንዲያገኝ የሚያደርገው ተሸከርካሪ ባለፈው የካቲት ወር በይፋ ሲመረቅ የአለምን ተመራማሪዎች ትኩረት በእጅጉ የሳበ ሆኗል፡፡
የማክስዌል ቺኩምቡትሶ የዚህ ክፍለ ዘመን መልክ ቀያሪው ፈጠራ በሚል እየተሞካሸ ነው፡፡ እንደ ቴስላ እና ሲሊከን ቫሊ ላሉ ኩባንያዎች ጆሮን ጭው የሚያደርግ የላቀ ፈጠራ ውጤት ሆኗል፡
ሴት ኤፍ ኢ ቪ ተሸከርካሪ ራሱን በራሱ ኃይል የሚሰጥ ከውጭ ምንም አይነት ግብዓት የማይጠቀም ይልቁንም የማይክሮሶኒክ ኢነርጂ ቁስ ብቻ የሚገጠምት አስገራሚ መኪና ነው፡፡

በ14 ዓመቱ ከሀይ ስኩል ያቋረጠው ማክስዌል ቺኩምቡትሶ ከመኪና ባለፈ በነዳጅም በኤሌክትሪክም የሚሰራ ሀይብሪድ ሄሊኮፕተር እንዲሁም በሬዲዮ ሞገድ የሚሰራ ቴሌቪዥንና ሞተር ብስክሌት ነው የሰራው፡፡
ሴት ቴክኖሎጂስ የተሰኘው የማክስዌል ተሸከርካሪ አምራች ኩባንያ በርካታ የምርት አቅርቦት ጥያቄዎች እየጎረፉለት ነው፡፡ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ አውቶሜትድ ጸረ ኢንፌክሽን መሳሪያ ሰራው ማክስዌል፣ የኢነርጂ ኮንቨርተር፣ የሰኪዩሪቲ እና ሌሎችንም መሳሪያዎች የፈጠረ ታምረኛ ሰው ነው፡፡
ከዓመታት በፊት የመመረዝ የሞት አደጋ አጋጥሞት እንደነበር የሚነገርለት የመኪና ፈጣሪው ማክስዌል አሁንም በርካታ ተቀናቃኞች እንደሉት እየተነገረ ነው፡፡ በፌስ ቡክ በኢሜልና በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች የግድያ ዛቻዎች እና የኢኮኖሚ ኪሳራ ማስፈራሪያዎች እንደሚደርሱት የሚናገረው ማክስዌል ከዚህ በፊትም በመሰል የኢነርጂ ዘርፍ ፈጠራዎችን ይዘው ብቅ ያሉ ሰዎች እንዲጠፉ ስላመደረጋቸው ያነሳል፡፡
ለዚህ ደግሞ አንድ ደቡብ ኮሪያዊ የታዳሽ ኃይል ቴክኖሎጂ ፈጣሪ ባልታወቀ መንገድ መገደሉን በምሳነት ያነሳል ማክስዌል፡፡
ያም ሆነ ይህ የቴክሎጂ ፈጠራው እውን መሆን የአለምን መልክ በመቀየር አፍሪካ ሌላ የእውቀትና የፈጠራ ከፍታ ስለመሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

