ለሩሲያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ስላለው የኢንቨስትመንት እድል ገለጻ ተደረገላቸው፡፡

Spread the love

ለሩሲያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ስላለው የኢንቨስትመንት እድል ገለጻ ተደረገላቸው፡፡

በትናንትናው እለት የኢትዮጵያ እና ሩሲያ የኢኮኖሚ ፎረም በሚሊኒየም አዳራሽ ሲካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ምስጋኑ አረጋን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ተገኝተዋል፡፡

ከሁለቱ ሀገራት የተውጣጡ የቢዝነስ አካላት የተገኙ ሲሆን በኢትዮጵያ ስላለው የኢንቨስትመንት አማራጭም ገለጻ ተደርጓል፡፡

ገለጻውን ያደረጉት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽንና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ናቸው፡፡

ዝግጅቱ ለ3 ቀናት ነው የሚካሄድ ሲሆን ኢትዮጵያም የብሪክስ አባል መሆኗ ሰፊ የንግድና ኢንቨስትመንት እድልን ለማስፋት እንደሚያረዳም  በፎረሙ ላይ ተጠቁሟል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *