የኢትዮጵያ_ ሩሲያ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል፡፡

Spread the love

የኢትዮጵያ_ ሩሲያ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት በተለያዩ ሁነቶች በሚካሄደው ዝግጅት ከሩሲያ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ ዓለም አቀፍ በርካታ ኩባንያዎች ታድመዋል፡፡

 የኢትዮጵያ የማዕድን፣ የግብርና፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ የቱሪዝም እና ሌሎች ዘርፎች የተውጣጡ ኩባንያዎችም በዝግጅቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

በዚህ ፎረም የሁለቱ ሀገራት ቢዝነሶች በጋራ በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

በፎረሙም የኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ በኢትዮጵያ ሩሲያ አምባሳደርና የሩሲያ ፌደሬሽን የንግድና ኢንዱሥትሪ ምክር ቤት ተወካዮችና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።

በኢትዮጵያ ስላለው የኢንቨስትመንት እና የንግድ እድል እንዲሁም በሩሲያ በኩል ስላለው ፍላጎት በዝግጅቱ መክፈቻ ላይ ቀርቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *