የለሚ ብሔራዊ ሲሚንቶ ፈብሪካ ተመርቋል፡፡

Spread the love

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ ዳርቻ የተንጣለለው ግዙፉ የለሚ ብሔራዊ ሲሚንቶ ፈብሪካ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ (ዶክተር) ተመርቆ በይፋ ሥራ ጀምሯል::

ኢንዱስትሪው ለአካባቢውና ለዞኑ ትልቅ የኢንቨስትመንት አቅም ከመሆኑም ባሻገር  የሀገሪቱን የሲሚንቶ እጥረት ችግር ይፈታል ተብሎ ይታመናል።

ለሚ ሲሚኒቶ ፋብሪካ በቀን ከ 10ሺ ቶን በላይ ሲሚንቶ የሚያመርት ሲሆን የኢትጵያን የሲሚንቶ ፍላጎት በሚገባ የሚሸፍን ይሆናል።

ይህ ግዙፍ ፋብሪካ በአማራ ክልል የመጀመሪያው የሲሚንቶ ፋብሪካ ሲሆን
በ125 ቢሊየን ብር (2.2 ቢሊየን ዶላር) ወጪ በኢስት አፍሪካ ሆልዲንግስ ከቻይና ባለሃብቶች ጋር ያስገነባው ፋብሪካው ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *